ለፅ/ ቤቱ አመራር እና ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ሠራተኛው መብቱ እዲከበርለት የሚፈልገውን ያህል ግዴታውን መውጣት ይኖርበታል ተባለ፡፡
ማክሰኞ የካቲት 30/2013 ዓ.ም
አዳማ ከተማ ኤከስኪዮቲቭ ሆቴል
በመንግስት ሰራተኞች መተዳደሪያ አዋጅን 1064/2010 እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጡ ደንቦችና መመሪያዎች፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅና በግዥ አፈፃፀም መመሪያ ላይ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ሰራተኞች ፣አመራር አካላት እና ወደ ተቋሙ ለተቀላቀሉ አዲስ ቅጥር ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ ፡፡
ከየካቲት 29 -30/2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ኤከስኪዮቲቭ ሆቴል የተሰጠው የዚህ ስልጠና ዋና ዓላማ በፐሊክ ሰርቪሱ መተዳደሪያ ህጎች፤በሠራተኞች መብትና ግዴታዎች እና በመንግስት ግዥና ንብረት አዋጅና በግዥ አፈጻፀም መመሪያ ላይ ግልጽ ግንዛቤ በመያዝ ለጋራ ተልዕኮ በጋራ በመሰለፍ የተቋሙን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡
ስልጠናውን አስመልክቶ ሰልጣኞች እደገለፁት በሲቪል ሰርቪሱ እና በግዥና ንብረት አፈጻጻም መመሪያ ላይ የተሰጠው ስልጠና ለሥራቸው አቅም በሚፈጥር መልኩ ጥሩ ግንዛቤና እውቀት እዳገኙበት ገልጸዋል፡፡
ስልጠናው የተሰጠው ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን እና ከመንግስት ግዥ ኤጅንሲ በመጡ ባለሞያዎች ነው፡፡
ስልጠናው በሁለት ተከፍሎ የሚሰጥ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር ስልጣኞች ሲጨርሱ የሁለተኛው ዙር ሰልጣኞች ይገባሉ፡፡
Previous post ታዳጊ ወጣቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማጎልበት የOutreaching ፕሮግራም
Next post ለኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቲክስ ቡድን በዶፒንግ ፅንሰ-ሃሳብ ስልጠና ተሰጠ::

Leave a Reply

Your email address will not be published.