በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር ለሚገኙ ፋርማሲ ባለሞያዎች ሲሰጥ ቆየው ትምህርታዊ ሴሚናር ተጠናቀቀ
የፋርማሲ ተቋማት ባለሞያዎች የፀረ-ዶፒንግ እቅስቃሴው አካል በመሆን ሙያዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እደሚጠበቅባቸው ተጠቆመ
’’የፋርማሲባለሞያዎች ከዚህ በኃላ የፀረ-ዶፒንግ አምባሳደሮቻችን ናችው፤ለሌሎች የሙያ አጋሮቻችው በቂ ግንዛቤ እዲኖራቸው በማድርግ ህገወጥ የመዳኃኒቶች ስርጭት እዳይኖር በማድረግ ረገድ የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣጥ እደሚገባቸው’’ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል ገለፁ፡፡
አቶ መኮንን ይህን የገለፁት በፀረ-ዶፒንግ እቅስቃሴው ረገድ ከኢትዮጵያ ፋርማሲ ባለሞያዎች ማህበር ጋር በቅንጅት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ እና በየደረጃው ባሉ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥና የፋርማሲ ባለሙያዎች ሚና አስመልክቶ ከህዳር 30-ታህሳስ 03 ቀን 2014 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው ሴሚናር ላይ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ነው ፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በማያያዝም ባለሙያው የዜጎችን ጤንነት በመጠበቅ ረገድ የሞራልና የህግ ግዴታ እንዳለበት ገልፀው ፤ በተለይም የፋርማሲው ባለሙያው ሙያውን ከሚያረክስ ተግባር በመራቅ፤ መድኃኒቶችና የፋብሪካ ውጤት የሆኑ ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ህጋዊ በሆነ መልኩ በሐኪም ትዕዛዝ ብቻ እንዲሰራጩ በማድረግ የህግ ጥሰቱን መከላከልና መቆጣጠር ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
በተለይ ህገ-ወጥ የሆነውን መንገድ በመምረጥ ያላግባብ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ኃላፊነት በጎደለው መንገድ የተከለከሉ አበረታች ቅመሞች እንዲሰራጩና ጥቅም ላይ እንዲውሉ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ተቋማትን ድርጊታቸውን በመቃወም፣ በማጋለጥና በኢንቨስትጌሽን ሥራ በመተባበር ረገድ ሙያተኛው የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እደሚወጣ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
’’በአለም አቀፍ የውድድር መድረኮች የተገነባውን የአገራችን መልካም ገፅታ ሲበላሽ፣ የዜጎቻችን ጤንነት አደጋ ላይ ሲወድቅ ሊያሳስበን ፤ሙያተኛውም ሊቆረቆር ይገባል ፤ ስፖርቱን እደ ዓይን ብሌን ልንጠብቀው ይገባል ፤ ስፖርቱ ለኢትዮጵያን ቅንጦት /Luxury/ አይደለም፣ የህይወትና የኢኮኖሚ ምንጭ ነው’’ ብለዋል፡፡
በፋርማሲ የሙያ መሰክ ለተሰማራችው ባለሙያዎች ግንዛቤ እድትጨብጡ ያስፈለገበትም ምክንያት የተጣለባችሁን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችላችውን እውቀትና በስፖረት አበረታች ቅመሞች መሰረታዊ ጉዳዮች፤ በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ሥርዓቶችና የህግ ማዕቅፎች ዙሪያ ግንዛቤ እዲኖራች ለማድረግ መሆኑን አቶ መኮነን አያይዘው ገልፀዋል ፡፡
በመጨረሻም ዋና ዳይሬክተሩ በተቋማችው ሙያው የሚጠይቀውን ሥነ-ምግባር በመጠበቅ የሙያውን ስምና ታማኝነት በማስከበር ሙያዊ ግዴታቸውን በአግባቡ በመወጣት አስተዋፆ ለማድረግ ማጤን እደሚገባቸው አሳስበዋል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *