ስፖርት ህክምና ባለሞያዎች አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በዘላቂነት በመከላከልና በመቆጣጣር ሥራዎች ላይ ኃላፊነታቸዉን አንዲወጡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ጥሪ አቀረቧል፡፡
በስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች (Supplements) ከዶፒንግ ላይ እና በተክለከሉ መዳኒቶች ዝርዝርዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡
ቅዳሜ የካቲት 21/2013
አዳማ ሄልዝ ሆቴል
ጽ/ቤቱ ጥሪዉን ያቀረበው በስፖርት ተቋማት ለሚሰሩ ለህከምና ባለሞያዎች፣ስነ-ምግብ እና ለወጌሻዎች‹‹ በአበረታች ቅመሞችና በሰፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች(Supplements)›› ዙሪያ ከየካቲት19-23/2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ነው፡፡
በስልጠናው ላይ ንግግር ያደረጉት የጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር በአገራችን ንፁህ ስፖርት እንዲስፋፋና በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው ውጤታማነት እንዲጎለብት እንዲሁም ዜጎቻችን ከስፖርቱ ማግኘት የሚገባቸውን ፍትኃዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የስፖርት ህክምና ባለሞያዎች ኃላፊነት ከፍተኛ እደሆን ገልፀዋል፡፡
የስፖርት የህክምና ባለሞያዎች አትሌቶችን በዶፒንግ ዙሪያ የማስተማር፤ሥነ-ባህሪ፣ሞራልና ዕሴቶችን በመልካም ጎኑ በመገንባት፤እራሳቸውን ከድርጊቱ በማራቅ ረገድ የሞራልናና የህግ ግዴታ እንዳለበት በመግለጽ አመራሩን ፣ አሰልጣኞችን ዶፒንግ በስፖርቱ ልማት ላይ የሚያስክተለውን ሁለንተናዊ ተፅዕኖ በማስተማር፣በማስገንዘብ የሚጠበቅባችሁን ኃላፊነት መወጣት እዳለባችው አስገንዝበዋል፡፡
በመጨረሻም ጽ/ቤቱ የዶፒንግ ህግ ጥሰት በሚፈጽሙ አትሌቶች ብቻ አይደለም ቅጣት የሚጥለው፤‹‹በቀጣይ በህክምና ባለሞያዎች ላይ ጭምር እርምጃ መውሰድ እደሚጀመር፡፡›› ጨምረው አሳስበዋል፡፡
በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ ከአዲስ አበባ፣ከኦሮሚያ፣ከደሬደዋና ከሀረሪ ክልል የተውጣጡ የስፖርት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ የህክምና ባለሞያዎች፣ስነ-ምግብ እና ወጌሻዎች የተሳተፉ ሲሆን በስፖርት ድጋፍ ሰጭ ምግቦች ከዶፒንግ ላይና በተክለከሉ መዳኃኒቶች ዝርዝርዝ እዲሁም ከዶፒንግ ጋር ያላቸው ዝምንድና በተመለከተ ስልጠና ተስጥቷል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን/ኢአፌ/ ከፍተኛ የህክምና ባለሞያ በሆኑት በወ/ሮ ቅድስት ታደሰ ነው፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *