በኢትየጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለሚገኙ ተተኪ አትሌቶች ስልጠና ተሰጠ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ በኢትየጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ለሚሰለጥኑ ባለተሰጦ አትሌቶች ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ‹‹በስፖርት አበረታች ቅመሞች ምርመራና ቁጥጥር (Testing) ›› ሂደት›› በሚል ዕርስ በአካዳሚዉ የስብሰባ አዳራሽ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የሥልጠናው ዓላማ ለተተኪ አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምንነት እና በተዘረጉ ያሰራር ሥርአቶች ዙሪያ ግንዛቤያችውን ለማሳደግ የተዘጋጀ መድርክ ነው፡፡
ስልጠናዉን የሰጡት በወ/ሮ መሰረት ተሾመ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህርና በጽ/ቤቱ የዶፒንግ ምርመራና ቁጥጥር ሲኒየር ባለሞያ (Senior DCO) ናቸዉ፡፡
በሥልጠናው ላይ የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ምርመራ፣በአለማቀፉ የምርመራና ቁጥጥር ስታነደርድ መሰረት (ISTI) በውድድር ጊዜ (In Competition) የሚደረግ ምርመራ፣የሽንትና የደም ናሙናዎችን በመሰብሰብ በWADA ወደ ተመዘገቡ ላቦራቶሪዎች የሚላክ ሰለመሆኑ፤ከውድድር ጊዜ ውጭ (Out of Competition) የሚደረግ ምርመራ ፤ በማንኛውም ጊዜና ቦታ የስፖርተኞች ምርመራ ሊካሄድ የሚችል መሆኑ፤ቅድሚያ መረጃ መስጠት የማይቻል መሆኑ፤በዚህ ስራ ስር የምርመራ ቋት (RTP)፣ የአድራሻ ምዝገባ (Whereabouts Information)፣ የምርመራ እቅድ (TDP) መከናወን የሚገባቸው ወሳኝ ተግባራት ስለመሆናቸው፣ ባለመያዋ አስረድተዋል፡፡
በመቀጠል ባለሞያዋ በገለፃቸዉ ምርመራ ቋት (RTP) በኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (ETH-NADO) እና በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ማህበራት ፌዴሬሽን (NADO) እደሚቋቋም፤ የምርመራ ቋት በየሶስት ወሩ የሚከለስ መሆኑን፤ በምርመራ ቋት (RTP) ውስጥ የተካተቱ አትሌቶች የማሳወቂያ ደብዳቤ (Notification) እንዲደርሳቸው እደሚደረግ ባለሞያዋ አያይዘዉ አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም አትሌቶች የተከለከሉ መድኃኒቶችን የመጠቀም ፈቃድ የሚያገኙት፣ከኢት/ብ/የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት (ETH-NADO) እና የአለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ (WADA) እደሆነ፤ በዚህም መሰረት በየደረጃው የህክምና ባለሞያዎችን የያዘና ራሱን የቻለ የTUE ኮሚቴ ስለመቋቋሙ፤አትሌቶች የተከለከሉ መድኃኒቶችን ለህክምና አገልግሎት ለመጠቀም የሚጠይቁበት በፎርም መኖሩን፤ ፎረሙ ከየት ማግኘት እደሚቻል፤አትሌቶች የተከለከሉ መድኃኒቶችን ለህክምና አገልግሎት ለመጠቀም የTUE ጥያቄያቸውን የሚያቀርቡበት ጊዜ፤ ከውድድር ከ30 ቀን በፊት ማቅረብ እደሚገባቸዉ ጨምረዉ አመልክተዉ፤ ጥያቄያቸውን የሚያቀርቡበት ዘዴ፤የመጠየቂያ ፎርሙን በመሙላት በTUE ኮሚቴው ኢ-ሜል፣ በአካል በመቅረብ በፀረ-ዶፒንግ ስራ አመራርና አስተዳደር ስርዓት (ADAMS) በኩል ማቅረብ የሚችሉ ስለመሆቸዉና በተያያዥ ርዕሶች ዙሪያ፤ ወ/ሮ መሰረት ተሾመ ሰፊ እና ዘርዘር ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ አድረገዋል፡፡
በስልጠናዉ ላይ ከ150 በላይ በተለያየ የስፖርት አይተቶች ስልጠና የሚከታተሉ ተተኪ አትሌቶች ተሳታፊ ሁነዋል፡፡
ስልጠናዉ ከግንቦት 27 – 28/ 2013 ዓ.ም ድረስ የቆየ ለሁለት ቀናት የተሰጠ ሲሆን በዶፒንግ ምንነት፤ በሚያስከትለው ጉዳት፤የህግ ጥሰት፤ተዘረጉ ያሰራር ስርዓቶች በሚሉና ተያያዥ ጉዳዮች በሚል ርዕስ በትናንትናዉ ዕለት ስልጠና መሰጠቱ የሚታወስ ነው፡፡