“በጋራ በመስራት ውጤታማ የሆኑ ስኬቶችን በተቋም ደረጃ ማስመዝገብ ይገባል” ክብር አቶ መኮንን ይደርሳል የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር
ቀን ፡- 08/05/2015 ዓ.ም
አዳማ ከተማ
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የ6 ወር የዕቅድ አፈጻጻም እና የቀጣይ 6 ወር ዕቅድ ከተቋሙ የስራ ክፍል ኃላፊዎች ጋር በነበረው የጋራ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው የአመራርነት አገልጋይ ክህሎት በመላበስ እንዴት ማገልገል ይቻላል በሚል ርዕስ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡
የተቋሙ አመራሮች የአገልጋይ አመራርነትን (servant leader) መርሆችን በመከተል ስራዎችን መስራት በተቋም ደረጃ ውጤታማ የሆኑ የጋራ ስኬቶችን ለማስመዝገብ ጠቀሜታ እንዳለው ክቡር አቶ መኮንን ይደርሳል ጠቁመዋል ፡፡
እንደ ዳሬክተሩ ገለጻ ግልጽ የሆነ ራዕይ በመያዝ ስራዎችን መስራት ፣ በባለቤትነት ስሜት በተቋም ደረጃ መንቀሳቀስ ፣ ለሰራተኞች ምቹ የሆነ የስራ ሁኔታዎችን መፍጠር እና በቡድን መስራት (Team work) አንድ አገልጋይ አመራር ሊኖሩት የሚገቡ ወሳኝ ነገሮች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም እንደ ተቋም ብቁና ተወዳዳሪ ሰራተኞችን በመፍጠር የአመራር መሪነት መገለጫዎችን ማዳበር እንደሚገባ አሳስበው ለዚህም የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የአገልጋይነት አመራርነት (servant leadership) መርሆችን የተላበሱ የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መፋጠር እንደ ተቋም የምንከተለው ስርዓት ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ በየትኛውም መስክ ተወዳድረው ማሽነፍ የሚችሉ ባለሙያዎችን መፍጠር የሚያስችሉ ስራዎችን አጠናክሮ በእንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *