አገር አቀፍ የስፖርት ማህበራትና የስልጠና መዕከላት የፀረ-ዶፒንግን ጉዳይ የእቅዳቸው አካል በማድረግና አስፈላጊውን ሐብት በመመደብ ትኩረት ሰጥተው መፈፀም እደሚገባቸው ተጠቆመ፡፡
መጋቢት 23/2013 ዓ.ም አዳማ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ETH-NADO/ ከኤፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለፌድራልና ከተማ አስተዳደር ለስፖርት አመራሮችና ለስልጠና ማዕከልት በዶፒንግ ዙሪያ የጋራ መድረክ በአዳማ ከተማ እያካሔዱ ይገኛሉ፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ከየክልሉ የተወከሉ የስፖርት አመራሮችና ከተለያዩ የስፖርት ማሰልጠኛዎች የተውጣጡ አካላት እየተሳተፉ የሚገኙበት ይህ ስልጠና በስፖርት አስተዳደር፣ በፀረ- ዶፒንግና በስፖርት ማርኬቲንግ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡
መድረኩን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል መልዕክት በማስተላለፍ በይፋ ከፍተውታል፡፡
በመቀጠልም ዋና ዳይሬክተሩ ክብር አቶ መኮነን ይደርሳል የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት አጀመመርና አሁን የደረሰበት ደረጃ በሚል በቀረበ ሰነድ ላይ ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ በገለጻአቸው የስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ የአገራችንን ስፖርት ሊያጠፋ የሚችል መሰረታዊ ችግር እንደሆነ፤የኢፌዲሪ መንግስት ይህን በአግባቡ በመገንዘብ ችግሩን ከመሰረቱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ እንደሚገኝ፤ በአገራችን እስካሁን ያለው አፈፃፀምም በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ፤ በቀጣይም ይህ እንቅስቃሴ በተጠናከረ መንገድ መቀጠል እደሚገባ ገልጸዋል :: አገር አቀፍ የስፖርት ማህበራትና የስልጠና ማዕከልት፤ ሌሎች ባለድርሻ አካላት የፀረ,ዶፒንግ ጉዳይን የእቅዳቸው አካል በማድረግና አስፈላጊውን ሐብት በመመደብ ትኩረት ሰጥተው መፈፀም የሚገባቸው መሆኑን አሰገንዝበዋል፡፡
አያይዘዉም የስፖርት ባለሞያዎች ከምንም በላይ ለሙያው ቅርብ በመሆናቸው በመጀመሪያ ራሳቸው ከችግሩ ነፃ በማድረግ የበኩላቸውን ገንቢ ሚና መጫወት የሚገባቸው መሆኑን አመልክተዋል፡፡
በመጨረሻም ቀደም ሲል በጀግኖች አትሌቶቻችን የተገነባውን የአገራችንን ስምና ዝና በአለም አቀፍ መድረኮች ለማስቀጠል ስፖርተኞች፣ የስፖርት ማህበራት እና የስልጠና ማዕከላትና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ያላሳለሰ ጥረት ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑን ዋና ዳይሬየክተሩ አቶ መኮነን አስግንዝበዋል፡፡
ከዚያ ባለፈ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር በዚህ ዓመት የፀረ አበረታች ቅመሞችን በተመለከተ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንዲካተት መደረጉን የብሔራዊ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮነን ይደርሳል ተናግረዋል፡፡ ይህም ታዳጊዎች ስለጉዳዩ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ግንዛቤው እንዲኖራቸው ያስችላል ብለዋል፡፡
ክምሳ ረዕፍት በኃላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ በፀረ-ዶፒንግ የህግ ማዕቅፍ ዙሪያ ለተሳታፊዎች ሰፊና ዘርዘር ያለ ገላፃ አድርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት በተለይ የስፖርት ስልጠና ማዕከላት ላይ ትኩረት አድርጎ በመስራት ወጣት ስፖርተኞችን ከአበረታች ቅመሞች መታደግ ይኖርበታል ሲሉ የስልጠናው ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደር የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ ም/ኮሚሽነሮች፣የስፖርት አካዳሚና ማዕከላት ዳይሬክተሮች፤ የፌድራል ስፖርት ኮሚሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች፣ የክለብ ስ/ አስኪያጀች በድምሩ 30 የሚሆኑ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ፡፡ ውይይቱ ከመጋቢት 23-25 ቀን 2013 ዓ.ም እደሚካሄድም ታውቋል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *