# ከዶፒንግ የጸዳ ስፖርት እና ስፖርተኞችን እናፈራለን !!!
በሐዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው ለስፖርት ማሰልጠኛ ተቋማት ስፖርተኞች አሰልጣኞች እና የስፖርት አካላት በዶፒንግ ዙሪያ እየተሰጠ ያለው የስልጠናና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ-ግብር እንደቀጠለ ነው ፡፡
ለሲዳማ ቡና አትሌቲክስ ቡድን አትሌቶች እና አሰልጣኞች በዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት ተሰጥቷል ፡፡
(ETH-NADO መጋቢት 16/2013 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ከ40 ለሚበልጡ አትሌቶች እና አሰልጣኞች በሀዋሳ ከተማ ሲዳማ ብልጽግና ፓርቲ አዳራሽ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡
በረጅም ፣ በመካከልኛ ፣ በአጭር ርቀት ሩጫ እና በዝላይ የሚወዳደሩ አትሌቶች ተሳትፈውበታል ፡፡
በስልጠና ፕሮግራሙ ላይ የጽ/ቤቱ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ መልዕክት አስታልፈዋል አገራችን የብዙ ጀግኖች አትሌቶች መፍለቂያ በመሆኗ እና በራሳቸው አቅም ተፈጥሮ በሰጠቻቸው በንጹህ ስፖርት ያስመዘገቧቸውን ወርቃማ ድሎችን በማየት ተተኪዎች አትሌቶች እራሳችሁን ከዶፒንግ በመጠበቅ የቀደሙ ጀግኖች አትሌቶቻችን ፈለግ መከተል ይገባችዋል በለዋል፡፡
በጽ/ቤታችን የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎችን በማሰልጠኛ ተቋማት በስፋት እየተሰራ በመሆኑ ይህን ስልጠና ለአትሌቶችሁ ከፍተኛ ጥቅም ያለው በመሆኑ በንቃት እንዲከታተሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ስልጠናው በትምህርት እና ስልጠና ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን በዶፒንግ ምንነት፣ ህግ ጥሰት፣የአትሌቶች መብትና ግዴታ፣ የዶፒንግ የምርመራ ሂደት እና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡:

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *