የስፖርት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ለህክምና ባለሞያዎች ዶፒንግ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተጀመረ ::
ቀን፡- አርብ የካቲት19፣2013 ዓ.ም
አዳማ ሄልዝ ሆቴል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ ETH-NADO/ ከ40 ለሚበልጡ ከአዲስ አበባ፤ ኮኦሮሚያ፣ ከድሬደዋና ከሀራሪ ለተወጣጡ የስፖርት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ለህክምና ፤ስነ-ምግብ እና ለወጌሻ ባለሞያዎች በአዳማ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠት ጀምረ፡፡
የስልጠናው ዓላማ በስፖርት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ የህክምና ባለሞያዎች በዶፒንግ ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ በስፖርት አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ እዲወጡ ለማስቻል ነው፡፡
የግንዛቤ ማሰጨበጫው በዶፒንግ ምንነት፤ የህግ ጥሰት፤ በስፖርትድጋፍ ሰጪ ስነ-ምግቦዎች (Supplements)፤በአሰራር ስርአቶች፤በአትሌቶች መብትና ግዴታዎች እና ምርመራና ቁጥጥር ሂደት፣የህግ ጥሰት ዙሪያ በጽ/ቤቱ ትምህርት፤ስልጠናና ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ባለሞያዎች ገለጻ ተደርገዋል፡፡
በከሰኃት በኋላ መርሃ-ግብር በቀረበው የመወያያ ሰነድ ላይ የቡድን ውይይት ከተደረገ በኃላ በቡድኑ ተወካዮች በኩል ለቤቱ ይቀርባል፡፡
ስልጠናው በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን በሰፖርት ስነ-ምግች (Supplements) ላይ ስልጠነና እዲሚሰጥ ታወቋል::