የባህልና ስፖርት ሚኒስተር አቶ ቀጀላ መርዳሳ የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣንን በዛሬው እለት ጉብኝት አደረጉ፡፡ በጉብኝቱ የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳን ጨምሮ የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ፣ የባሕልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ወርቅነሽ ብሩ በጉብኝቱ ተገኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣንን አጠቃላይ እንቅስቃሴና እየተሠሩ ስላሉ ሥራዎች በዋና ዳይሬክተሩ በአቶ መኮንን ይደርሳል ገለፃ ተደርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን ይደርሳል፣ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኸኝ ፣የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቦርድ ሰብሳቢ ፕ/ር አክሊሉ አዛዥ እና የጽ/ቤቱ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡