የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/Eth-Nado/ ለአመራሮችና ለባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በአዳማ በመሰጠት ላይ ነው።
በዛሬዉ ዕለት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የ10 ዓመት ፍኖተ ካርታ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተስጥቷል ፡፡
ዛሬ መስከረም 14 ቀን 2014 ዓ.ም
በአዳማ ከተማ የተጀመረው የውይይት መድረክ እስከ መስከረም 16/ 2014 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን 10 ዓመት ፍኖተ ካርታ ላይ ለአመራሮችና ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የመንግስት ቁልፍ ተልዕኮ የዜጎችን ልማት ማረጋገጥ ሲሆን ዋና እሴቶቹም የተገልጋይ መብቶች ወይም ፍላጎቶች ናቸው፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እንዳሉት በየትኛውም የመንግስት ተቋም የሚሰራ ሲቪል ሰርቫት የአገልጋይነት መንፈስን የተላበሰ ፣ብቃት ያለው፣ገለልተኛ፣ በስነ-ምግባሩ የተመሰገነና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብን በመያዝ በሚሰጠው አገልገሎት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በተጨማሪ መሪ ባለራዕይ፣ጠንካራ ስሜትና ፍላጎት ያለው፣አዲስ ሀሳብ አፍላቂ፣ፈጣሪ፣ቀስቃሽ፣አሳታፊ፣የሌሎችን ጥቅም የሚያስቀድም፣ለለዉጥ ዝግጁ የሁነና ለውጥ አምጪ መሆን እንዳለበት አብራርተዋል ፡፡
በፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅንሰ-ሃሳብና በተዘረጉ አሰራር ስራቶች፤ በሲቨል ሰረቪስ ደንቦችና መመሪያዎች፣አዋጆችናበፋይናንስ አሰራር ስርአቶችና መመሪያዎች ዙሪያ ስልጠና እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
የስልጠናው ዓይነት ዳግም ስልጠና (Re-training) ሲሆን ወደ ጽ/ቤቱ ለተቀላቀሉ ለአዲስና ነባር ሰራተኞች ተስጥቷል፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *