የፀረ-ዶፒንግ የግንዛቤ ማስጨበጫ Outreaching ፕሮግራም በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ትንሿ ስታዲያም ተካሄደ ፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን (ETH-ADA) ከታህሳስ 20-23/2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በትንሿ ስታዲያም በሚካሄደው የ1ኛው ዙር የብሔራዊ የክለቦች የቦክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ስፖርተኞችና የስፖርት ባለሞያዎች እንዲሁም የስፖርቱ ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የOutreaching ፕሮግራም እያካሄደ ይገኛል፡፡
በዚህ ውድድር ላይ የተለያዩ የቅስቀሳና ፕሮሞሽን ማቴሪያሎች ፤ ብሮሸሮች ፣ ለስፖርተኞች ፣ ለቦክስ ስፖርት ባለሞያዎች ፣ ለቦክስ ስፖርት አሰልጣኞ እና ለሌሎች ተሳታፊዎች የተሰራጨ ሲሆን አሳታፊ የሆኑ በቀላሉ ግንዛቤ እንዲጨብጡ የሚያስችል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሂዷል ። እንዲሁም የተለያዩ መልዕክት የሚያስተላልፉ ባነሮች ተዘጋጅተው ለዕይታ በሚያመች ቦታዎች እንዲሰቀሉ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን የሚመልከቱ መልዕክቶችን በፕሮግራም አስተዋዋቂዎች አማካኝነት ለተሳታፊዎች እንዲተላለፉ ማድረግ ተችሏል ::
በውድድሩ ከተለያዩ የቦክስ ክለቦች የተወጣጡ የወንድ እና የሴት ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል፡፡.