አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ ለማጎልበት የግንዛቤና ማሳደጊያና የቅስቀሳ የOutreaching ፕሮግራም በአዲስ አበባ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
The Ethiopia Anti-Doping Authority (ETH-ADA) has launched an Outreaching program at the ongoing Ethiopian Athletics Tournaments in Addis Ababa to raise awareness among athletes, support professionals, and sports leaders. It is also said that it will create mass mobilization against doping among the sports community.
ቀን፡- ታህሣሥ 13/2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን (ETH-ADA) በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን አዘጋጅነት ከታህሣሥ
13 -17 ቀን 2014 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚው በ ሚካሄደው የአጭር፣ መካከለኛ፣ 3,000 ሜትር መሰናክል፣ የርምጃና የሜዳ ተግባራት ውድድር ላይ አገራችውን በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች የሚወክሉ አትሌቶች፣ የስፖርት ባለሞያዎችን፣ የስፖርት አመራሮን፣ የስፖርት ህክምና ባለሞያዎችንና የስፖርቱን ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ እና ሰፊ ንቅናቄ ለመፍጠር የፀረ-ዶፒንግ የግንዛቤ ማሳደጊያና የቅስቀሳ የOuteraching ፕሮግራም ማካሄድ ጀምሯል፡፡
በOutreaching ፕሮግራሙ ላይ አትሌቶች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ በቀላሉ ግንዛቤ እንደሚጨብጡ፣ ዕውቀት እዲይዙ የሚያስችላቸውና አትሌቶች የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉበት በ ኮምፒዩተር የታገዘ ጥያቄና መልስ ውድድር፤ የተለያዩ መልዕክት የሚያስተላልፉ በሰሌዳ የሚሰቀሉ ባነሮች፤ እዲሁም ለተሳታፊዎች የፀረ-ዶፒንግ መልዕክቶች የያዙ ብሮሸሮች ተሰራጨተዋል ፡፡
በ Outreaching ፕሮግራም ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች በቀጣይ አገራቸውን በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች የሚወክሉ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ይህ ፕሮግራም የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን የስፖርቱን ማህበረሰብ በዶፒንግ ዙሪያ ያለው ግንዛቤ ከማጎልበት አኳያ ከሚሰጣቸው ሥልጠናዎች ባሻገር በተለያዩ አገራቀፍ ውድድሮች መሰረት በማድረግ የትምህርትና ቅስቀሳ ፓኬጆችን በመጠቀም የግንዛቤና የንቅናቄ ስራዎችን በማካሄድ በስፖርት አበረታች ቅመሞች/ ዶፒንግ ዙሪያ የአስተሳሰብ ለውጥ እዲመጣ ጠንክሮ በመስራትላይ ይገኛል ፡፡

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *