በተለያዩ አለም አቀፍ ውድድሮች ላይ አገራችንን በመወከል እና በግላቸው ለሚሳተፉ አትሌቶች እና ለተተኪ ስፖርተኞች በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ዙሪያ ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችል ስልጠና በደብረ በርሃን ከተማ አተሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ተሰጠ ፡፡
ቀን፤ሀሙስ ጥቅምት 04/2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን /ETH-NADA/ በደብረ ብርሃን ከተማ አሰተዳደር ለስፖርት ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች እዲሁም ለተተኪ አትሌቶች ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
የግዛቤ ማስጨበጫው ዓላማ በዋናነት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ እና በየደረጃው በተዘረጉ ያሰራር ሥርአቶች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ሲሆን እዲሁም የስፖርት ባለሞያዎችና ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች ግንዛቤ ጨብጠው የዶፒነግን ጉዳይ በስልጠና ማኑዋሎቻቸው ውስጥ አካታዉ ተግባራዊ ለማድረግ በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ አትሌቶች ከግንዛቤ ባለፈ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻልና ችግሩን በዘላቂነት በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የድርሻውን እንዲወጣ ማስቻል ነው፡፡
በዛሬው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ወይም የፀረ-ዶፒንግ የስልጠና ውሎ ላይ የአትሌት ማናጀሮች፣አትሌቶች ተሳታፊ ነበሩ፡፡ በዚህ መድረክ ላይ በዋናነት አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ የስፖርት አበረታች ቅመሞችን ወይም ዶፒንግን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የስፖርት ባለሞያዎችና የአትሌቶች ተወካዮች ድርሻ ምን መሆን እንዳለበት ውይይት ተደርጓል፡፡
በስልጠናው የዶፒንግ ታሪካዊ አመጣትና ምንንነት፣ተቋማዊ አደረጃጀት፤ የህግ ጥሰት፣ የአትሌቶች መብትና ግዴታዎች፤በሚያስከትሉት ጉዳቶችና በድጋፍ ሰጪ ምግቦች ላይ በተመለከተ የጽ/ቤቱ የትምህርት፣ስልጠና፣የህዝብ ንቅናቄና የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በአቶ ፈለቀ ዋለልኝ የተሰጠ ሲሆን፤ በምርመራና ቁጥጥር ሂደት፣እንዲሁም በአትሌቶች መብቶችና ግዴታዎች ዙሪያ በአቶ ዳንኤል ተስፋዬ የትምህርት፣ስልጠና፣የህዝብ ንቅናቄ ቡድን መሪ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በመድረኩ ላይ ከ80 በለይ የአትሌት ድጋፍ ሰጨጭ ባለሞያዎችና አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
Ethiopia National Anti-Doping Authority (ETH-NADA) has provided awareness creation trainings for athlete support personnel and Athletes drown from Debre Birhan city administration Youth Training Center and Manager Team Athletes .
Different topics of doping particularly on the current status of Ethiopia on the fighting against doping, issues like History and Concept of doping, Organizational structure and Testing Procedures, Anti-Doping Rule Violations, Consequences of Doping, Roles and Responsibilities of athletes and Athlete Support Personnel for the athletes included in the IF and ETH-NADA Registered Testing Pool (RTP) and youth training center Athletes .
The training is expected to create a vital capacity to implement the Anti-Doping training manual at the youth training center.