ዶፒንግን ጉዳይ በፎካል ፐርሰን ደረጃ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ ETH-NADO/ ግንቦት 22/2013 ዓ.ም ከአማራ ክልል የስፖርት ኮሚሽን የስራ ክፍል አመራሮችና ከስፖርት ህክምና ባለሞያዎች ጋር በኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ ዉይይት ተካሄደ፡፡
በሥልጠናው የማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡርት ወ/ሮ ፋንታዬ ገዛኽኝ እንደተናገሩት፤ስልጠናዉ ከአማራ ክልል የስፖርት ኮሚሽን ጋር በቅንጅት ሲዘጋጅ በዋናነት በስፖርት አበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግን በየደረጃው በተዘረጉ የአሰራር ስርአቶች፤የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በማሰብ ሲሆን ባለድርሻ አካላት የሚጠተቅባቸዉን ኃላፊነት እዲወጡ ግንዛቤቸዉን በማጎልበት ችግሩን በዘላቂነት ለመከላከልና ንፅህ ስፖርትን በማሰፋፋት ረገድ የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ተወካይ አቶ ምትኩ አክሊሉ እደተናገሩት የዉይይት መድረኩ ዋናዉ የዶፒንግን ጉዳይ የሚመለከት በጽ/ቤት ደረጃ ይኑር አይኑር ሳይሆን፤የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እደሚገባ ፤የዶፒንግ ጉዳይ ስተራቴጂካል በሆነ መንገድ መመራት እዳለበት፤ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን የዶፒንግን ጉዳይ በፎካል ፕረሰን ደረጃ እስከ ታችኛዉ መዋቅር ድረስ ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ፤የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በቀጣይ በጀት ዓመት በዕቅድ ዉስጥ ተካቶ እደሚሰራ፤የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን አስታወቋል፡፡
ጽ/ቤቱ ዶፒንግን ለመከላከልና ለመቆጣተር በተለይ በበጀት ዓመቱ በርካታ ሥራዎች የተሠሩ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ የትኩረት ቡድኖችን (Target group) በመለየት ስልጠና መስጠት፤ ለህክምና ባለሞያዎችን፤ ለክለብ አሰልጣኞችን፣ ለቴክኒክ ኃላፊዎች.፣ ለስፖርት ማህበራት፣ ለቤት ኪነግ ፕሪሜር ሊግ ተጫዋቾች.፣አስልጣኖችን፣አመራሮችንና ሌሎች አካላትን ግንዛቤ ማስጨበጥ የሚሉት እንደሚገኙበት አመልክተዋል ፡፡
ተሳታፊዎችም፣የተሰጠው ስልጠና ጥሩ እደነበረና ጽ/ቤቱ ታዳጊ ወጣቶች፤ፕሮጀክቶች ላይ እና የ TOT ስልጠና ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እዳለበት ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻ ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ የአማራ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ስልጠናዉ እዲሳካ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡