በአሰላ ከተማ እየተካሄደ ያለው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ግንዛቤ እና ህዝባዊ ንቅናቄ (Social Campaign ) ፕሮግራም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን በአሰላ ከተማ የሚያካሂደው የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ እና ህዝባዊ ንቅናቄ ፕሮግራም በዛሬውም ዕለት በ4ኛው የኦሮሚያ ከ16 ዓመት በታች እና ከ18 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ስፖርተኞች እና የስፖርት ባለሙያዎች እንዲሁም ለውድድሩ ተመልካቾች የፀረ-ዶፒንግ ግንዛቤ ማሳደግ እና የንቅናቄ ስራ አጠናክሮ ቀጥሏል ፡፡
የፀረ-አበረታች ቅመሞች ግንዛቤ እና የህዝብ ንቅናቄ (Social Campaign) ፕሮግራሙን በድንኳን ውስጥ እና በስታዲየም ውስጥ ለውድድሩ ታዳሚዎች እና ተሳታፊዎች በዶፒንግ ዙሪያ መልዕክቶች በማይክራፎን የተላለፉ ሲሆን በተጨማሪም በአማርኛ እና በኦሮምኛ የተዘጋጁ ብሮሸሮች ፣ ቲሸርቶች ማሰራጨት ጨምሮ በባነር መልክ የተዘጋጁ የተለያዩ የፀረ-ዶፒንግ መልዕክቶች በስታዲያም ውስጥ ተሰቅለዋል፡፡
የፀረ-አበረታች ቅመሞች ህዝባዊ ንቅናቄ እንቅሳቃሴ ከፊል ገፅታ

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *