የመጀመሪያ ደረጃ የአሰልጣኝነት ስልጠና ለሚከታተሉ የስፖርት መምህራን በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒነግ ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ፡፡
የስፖርት መምህራን ስፖርተኖችን ከማሰልጠን ጎን ለጎን የዶፒንግን ጉዳይ አካተው ማስተማር እዳለባቸው ተጠቆመ ፡፡
ጽ/ቤቱ/ETH-NADO/Sport Teachers Should play their role to the fight against Doping :
ETH-NADO Anti-Doping training has started to providing for Regional states sport teachers.
ሀሙስ ግንቦት19/ 2013 ዓ.ም
በባህር ዳር ከተማ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት/ ETH-NADO/ ከአማራ ክልል ለተወጣቱ የአንደኛ ደረጃ የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ለሚሳተፉ የስፖርት መምህራን ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት የሚቆይ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ዙሪያ ስልጠና በባህር ዳር ከተማ መሰጠት ተጀመረ፡፡
ስልጠናዉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ፅ/ቤት /ETH_NADO/ እና የኤፌድሪ ትምህርት ሚኒስተር በጋራ ያዘጋጁት መድረክ ነው፡፡
ስልጠናው የሚሰጠው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስፖርት አካዳሚ አዳራሽ ነው፡፡
የሥልጠናው ዓላማ የስፖርት መምህራን ዶፒንግን ለመከላከልና ንፁህ ስፖርት ለማስፋፋት በሚደረገውን ጥረት ላይ ግንዛቤ ፈጥረው ስፖርተኞችን ከማሰልጠን ጎን ለጎን የዶፒንግን ጉዳይ ማስተማር እዲችሉ አቅም ለማጎልበት የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡
በሥልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ መኮነን ይደርሳል “እደተናገሩት፤፡በአሁኑ ሰዓት ስፖርቱን ማልማት፣ ስፖርተኞችን ማሰልጠን ብቻዉን በቂ አይደለም፤ ስፖርቱ ከዶፒንግ ችግር ነፃ መሆን ይኖርበታል ፤ ስፖርትኞችን ሥታሰለጥኑ፣ ስታበቁ፣ የዶፒንግን ጉዳይ አካታችው ማስተማር፣ግንዛቤ መፍጠር ዋነኛ ሥራችው ልታደርጉ ይገባል፡፡” ብለዋል
ስፖርቱ አዳጋ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ሰፖርታችንን ከሚያጠለሽ ነግር ነፃ እናድርግ ፡፡ በማልት ጥሪ አስተላልፈዋል ዋና ዳይሬክተሩ፡፡
በመጨረሻ ከሁሉም በማስቀደም በመካከላችሁ ተገኝቸ ይህን መልዕክት ማስተላለፍ በመቻሌ የተሰማኝን ልባዊ ደስታ ለመግለፅ እወዳለሁ ካሉ በኃላ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ መኮነን ፤የተዘጋጀውን ስልጠና በትኩረት እድትከታተሉ አድራ ጭምር አስተላልፋለው በማለት መድረኩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
በሥልጠናው ላይ በአበረታች ቅመሞች ወይም ዶፒንግ ታሪካዊ አመጣጥ፣በሚያስከትላቸው ጉዳቶች፣የዶፒንግ ህግ ጥሰት እና በተያያዥ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
በስልጠናው ላይ ከ90 በላይ የሁኑ ከአማራ ክልል ከተለያዩ ት/ቤቶች የተውጣጡ የሁለተኛ ደረጃ የስፖርት መምህራን ተሳትፈዋል፡፡
ስልጠናው በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን፣ በቀረበው ሰነድ ላይ በቡድን ውይይት ከተደረገበት በኃላ በቡድኑ ተወካዮች ለቤቱ ግለፃ ይደርጋል ፡፡
May be an image of 7 people, including Redae Gebrekidan, people sitting and people standing

By Ermias

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *